የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የግንባታ ማሽነሪዎች በማስመጣት እናቀርባለን፡፡ የምናስመጣቸው ማሽነሪዎች በጥራታቸው አስተማማኝ፣ ለሀገራችን መልክአምድር ተስማሚ ናቸው፡፡ ታዋቂ የንግድ ምልክት ያላቸው ኤክስካቫተሮች፣ ሎደሮች፣ ቡልዶዘርሮች እና ሌሎችንም ዓለም ዓቀፍ እውቅና ካላቸው አምራቾች እናመጣለን። ቀልጣፋና አስተማማኝ ከሆነው አቅርቦታችን በተጨማሪ ከሽያጭ በኋላ ያለን የጥገናና አቅርቦት አገልግሎት በደንበኞቻችን ዘንድ ተመራጭ እንድንሆን ያደርገናል፡፡

በቤአኤካ፣ እንከን የለሽ ሥራዎችን በመጠበቅ የመለዋወጫ ዋና አስፈላጊነት እንገነዘባለን። ሁሉንም የመለዋወጫ መስፈርቶችዎን ለመፍታት የእናንተ ጽኑ አጋር ነን። ለጥራት እና ለውጤታማነት ያለን የማያወላውል ቁርጠኝነት የሚፈልጉትን ትክክለኛ ክፍሎች በፍጥነት ማድረስ ያረጋግጣል፣ ሁሉም በተወዳዳሪ ዋጋ። በእኛ ሰፊ ክምችት እና ቴክኒካል ብቃታችን ምርታማነትን በማሳደግ የስራ ጊዜን ለመቀነስ እናግዛለን።
የድርጅታችን ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአስመጪነት የንግድ ዘርፉ ከፍተኛ እውቀትና ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተደራጀ ነው። በዚህም የግንባታ ማሽነሪዎች፣ የግንባታ ግብዓቶች፣ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ግብአቶች (ለድርጅታችን ፋብሪካዎችና ለሌሎችም እናቀርባለን፡፡ የተለያዩ ኬሚካሎች፣ የሱፍ ድፍድፍ ዘይት፣ ለማዕድን ልማት ፋብሪካዎች ፍጆታ የሚውሉ ግብአቶች፣ መለዋወጫዎች እና ሌሎችንም በማስመጣት ላይ እንገኛለን፡፡
የጭነት መኪናዎች እና መለዋወጫዎች አስመጪ እና አከፋፋይ ስንሆን መኪናዎቹን በጥሩ ሁኔታ በተደራጁት ተቋሞቻችን ውስጥ የመገጣጠም ስራም ተጠቃሽ ነው፡፡ የነዳጅ ጫኝ መኪኖች፣ የጭነት መኪናዎች፣ ሌሎች ምርቶች እንዲሁም መለዋወጫዎችን እናስመጣለን፣ እንገጣጥማለን፡፡
እንዲሁም መለዋወጫዎች ናቸው። ቤአኤካ በአሁኑ ጊዜ የተለያዩ ከባድና ቀላል የግንባታ ማሽነሪዎችን ከውጭ ያስመጣል፡፡ ከነዚህም ውስጥ፡- ግሬደር፣ ኤክስካቫተር፣ ሎደር፣ ሮለር፣ ክሪሸር፣ ቡልዶዘር እና ገልባጭ መኪናዎች ለምሳሌ እንደ ሻክማን፣ ሲኖ፣ የውሃ መኪና፣ መለዋወጫ እና የብረታ ብረት ለድርጅቱ አገልግሎት እና ለሽያጭ ያቀርባል፡፡
ከውጭ የምናስገባቸው ማሽነሪዎች የታወቀ ስም ያላቸው፣ በኢትዮጵያ የተለያዩ መልክአ ምድሮች ላይ ውጤታማነታቸውና ብቃታቸው የተረጋገጡ እንዲሁም በበቂ ሁኔታ ተደራሽነትና ከሽያጭም በኋላ በመለዋወጫ አቅርቦትና ክትትል የሚደረግላቸው ናቸው።
ድርጅታችን ለተሽከርካሪዎች እና ለግንባታ ማሽነሪዎች ትክክለኛ መለዋወጫ በማስመጣት እና በማቅረብ የታወቀ ነው፡፡
መሰረታዊ አላማችን ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የግንባታ ማሽነሪዎች እና ከባድ የግንባታ መሳሪያዎችን ማቅረብ እንዲሁም ትክክለኛ መለዋወጫዎችን ማስመጣት እና ማቅረብ ነው።
እንዲሁም 60/70፣ 85/100፣ 120/150፣ 180/200 እና ሌሎች ደረጃዎች ያሏቸውን 100% ንፁህ የመንገድ ግንባታ ሬንጅ አስመጥተን እናሰራጫለን።
ቤአኤካ ከ6 ሚ.ሜ እስከ 32 ሚ.ሜ ድረስ የተለያየ መጠን ያላቸውን ብረቶች (ፌሮ) የሚያስመጣ ሲሆን እነዚህ ምርቶች በዋናነት ከቱርክ የሚገቡ ናቸው።