ፋብሪከችን በአማራ ክልል ባህርዳር የሚገኝ ሲሆን, ዘመናዊ ቴክኖሎሀጂን በመጠቀም ከጣሊያን ባስመጣነው መሳሪያ የተለያዩ መጠን ያለውን እብነበረድ በተለያየ መጠን እያመረተ ለገበያ ያቀርባል፡፡
በኢንዱስትሪ ዘርፉ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ጥበብ የተመሰረተ የማምረቻ ፋብሪካ ሲሆን በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ይገኛል፡፡ ከማዕድን ማውጫ ሳይት የሚመጡትን የተለያየ ቀለምና ቅርጽ ያላቸው የግራናይት አይነቶችን ወደ ፋብሪካችን በመላክ በደንበኞች ፍላጐት መሰረት እያቀረብን እንገኛለን፡፡ በከፍተኛ መጠን፣ ፍጥነትና ጥራት የማምረት አቅሙ የሚታወቀው ፋብሪካችን በአዲስ ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ጥራት ያለውን ምርት በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶቹን ለገበያ ያቀርባል፡፡
ፋብሪከችን በአማራ ክልል ባህርዳር የሚገኝ ሲሆን ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከጣሊያን ሀገር ባመጣነው ከፊል-ሮቦቲክ ቴክኖሎጂ ዲዛይን የተደረገ ሲሆን ይህም ለሀገራችን በአይነቱ የመጀመሪያው ነው፡፡ ያለውን እብነበረድ በተለያየ መጠን እያመረተ ለገበያ ያቀርባል፡፡
ፋብሪከችን እ.ኤ.አ. በ2016 ዓ.ም. በባህርዳር የተቋቋመ ፋብሪካ ሲሆን ከአዲስ አበባ 552 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ኮከብ ቀለም ፋብሪካ የግድግዳ ቀለም፣ የዝገት መከላከያ ቀለም /Anti-rust እና ኳርትዝ ቀለም ምርቶችና ሌሎችንም በማምረት የገበያውን አቅርቦት ክፍተት ለመሙላት ትልቅ አቅም ያካበተ ፋብሪካ ነው፡፡ የውስጥ እና የውጪ ግድግዳ ቀለሞች፣ ሌሎች የውሃ እና ሴንቴቲክ ቀለሞች፣ ኳርትዝ ፣ የዝገት መላከያ ቀለሞች ዋና ዋናዎቹ ምርቶቻችን ናቸው፡፡
የፋብሪካችን ማሽኖች እና የላቦራቶሪ መሳሪያዎቻችን በዘርፉ ዘመናዊ የሚባሉት ምርጥ ቴክኖሎጂዎች ሲሆኑ ሁሉም ከአውሮፓ ያስመጣናቸው ናቸው፡፡ በምንጠቀማቸው ዘመናዊ መሳሪያዎች፣ በምርት ሂደታችንና በጥራታችን ምክንያት ምርቶቻችን የታወቁና በገበያ ውስጥ በሰፊው የሚመረጡ አድርጓቸዋል፡፡ የምርት ጥራታችንን ሁሌም ዘላቂ በሆነ መንገድ በማሻሻል፣ የደንበኞችን እርካታ በማሟላት ቀዳሚ ሆኖ መቀጠልን መርሀችን አድርገን በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን፡፡
ቦታ፡ አማራ ክልል ባህር ዳር & አዲስ አበባ ሀናማርያም ሳይት.
የኳርትዝ ምርታችን በዘመናዊ የአመራረት ጥበብ የተመረተና ረዥም ጊዜ በጥራት በማገልገል ወደር የማይገኝለት በመሆኑ በደንበኞቻችን ዘንድ ተመራጭ ነው፡፡ አለምአቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለደንበኞቻችን ከምናቀርባቸው ምርቶች አንዱ የሆነውን የኳርትዝ ምርት በመጠቀም ግንባታዎች የምርታችንን ውበት ለብሰዋል፡፡