News

None

በቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ የተ/የግ/ማህበር  እየተገነባ የሚገኝው #የገበታለሀገር አንዱ አካል የሆነውን ጎርጎራ ፕሮጆክት

Oct. 18, 2022

በቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ የተ/የግ/ማህበር  እየተገነባ የሚገኝው #የገበታለሀገር አንዱ አካል የሆነውን ጎርጎራ ፕሮጆክት ጠቅላይሚኒስትርዐቢይአሕመድከከፍተኛየመንግሥትአመራሮችጋርበመሆንየልማትፕሮጀክትንየሥራክንውንጎብኝተዋል።


Read More
None

በሶማሊ ክልል ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ በጀት እየተገነባ ያለው የጅግጅጋ–ገላልሼ–ደገህመደው- ሰገግ የአስፓልት መንገድ

Sept. 6, 2022

በሶማሊ ክልል ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ በጀት እየተገነባ ያለው የጅግጅጋ–ገላልሼ–ደገህመደው- ሰገግ የአስፓልት መንገድ በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ገለጸ


Read More
None

ሀገር አቀፍ ተቋራጭ በሆነው የ”ቤአኤካ ” ድርጅት እየተገነባ ያለው የ110 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ግንባታ ምንጭ:- ኢዜአ

Sept. 3, 2022

ጅግጅጋ፤ ነሐሴ 26/2014(ኢዜአ) ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ በጀት የሚገነባው የጅግጅጋ – ገላልሼ – ደገህመደው- ሰገግ ያለው የ110 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ግንባታ በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ገለጸ።

ከመንገዱ አጠቃላይ ግንባታ እስካሁን 41 በመቶ መከናወኑ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የፕሮጅክቱ ተቆጣጣሪ ኢንጂነር እዝራ ሽብሩ ለኢዜአ እንዳሉት፤ “የጅግጅጋ – ገላልሼ – ደገህመደው- ሰገግ መንገድ አስተዳደሩ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚያስገነባቸው አስፓልት መንገዶች አካል ነው።

ሀገር አቀፍ ተቋራጭ በሆነው የ”ቤአኤካ ” ድርጅት እየተገነባ ያለው መንገድ  በሚቀጥሉት አንድ ዓመት ከሥምንት ወራት ውስጥ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ስራ እየተፋጠነ  መሆኑን ገልጸዋል።

መስሪያ ቤታቸው ፕሮጀክቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ለተቋራጩ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ያመለከቱት ኢንጂነር እዝራ ፤ በክልሉ ተከስቶ የነበረው ድርቅ ተከትሎ የተፈጠረው የውሃ እጥረት የመንገዱን የስራ እንቅስቃሴ እንደፈተነው  አንስተዋል።

ሆኖም የውሃ ችግሩን ለመፍታት አማራጭ የዝናብ ውሃ ማሰባሰቢያ ኩሬ በማዘጋጀት ከፕሮጀክቱ በተጓዳኝ የአካባቢ  አርብቶ አደር የቤት እንስሳት እንዲጠቀም በማድረግ አስተዳደሩ ማህበራዊ ኃላፊቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ተቋራጩ የ”ቢኤካ ” ድርጅት የፕሮጅቱ ስራ ኢስኪያጅ ኢንጂነር ሐጎስ መኮንን በበኩላቸው፤ የመንገድ ግንባታው ከተጀመረ አንድ ዓመት ከአስራ አንድ ወር መሆኑን ጠቅሰው፤ “አስካሁን   የአፈር ቆረጣ ፣ ድልድይ ግንባታ፣ የግንባታ ግብአቶች ማምረትና ዝግጅት እንዲሁም የውሀ መፋሰሻ ቱቦዎች ማምረት ስራ ከ80 ከመቶ በላይ ተከናውነዋል”ብለዋል ።

መንገዱ በፋፈን፣ ደገህቡርና ፊቅ ዞኖች በሚገኙ  የአርብቶ አደር መንደሮች እና የወረዳ አስተዳደር ማዕከላትን በማገናኘት መንግስት የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የጎላ ጠቀሜታ ይኖሯል ነው ያሉት።

በተለይ  የእንስሳት ሀብት ማዕከል የሆኑና ቀደም ሲል መንገድ ያልነበራቸው አካባቢዎችን በቀጥታ ጅግጅጋና ጎዴ ከተሞችን ከሚያገናኘው ዋናው መንገድ ጋር በደናን ከተማ በኩል በአቋራጭ በማስተሳሰር የእንስሳት ንግድ ለማቀላጠፍ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ አንድ ሺህ ያህል ዜጎች የስራ እድል ማስገኘቱን የጠቀሱት ስራ አስኪያጁ፤ ለአካባቢው ህብረተሰብም የድርጅቱ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት መስጫ ተሽከርካሪ እንዲጠቀም ከማመቻቸት ሌላ አስራ አንድ የዝናብ ውሃ ማሰባሰቢያ ኩሬዎች ቆፋሩና ግንባታ በራሱ ወጪ በመስራት ድርቁ የከፋ ጉዳት እንዳያርስ እያገዘ መሆኑን ገልጸዋል።

የመንገድ ግንባታው በሚያገናኛቸው ከተሞች የተሻለ ትራንስፖርት ተጠቃሚ በማድረግ የአርብቶ አደሩን  ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ያቀላጥፋል   ያሉት ደግሞ የፕሮጀክቱን ስራ የሚያማክረው  የ” ሲ ቴች ኢንጅንሪንግ ” አማካሪ መሃንዲስ ኑሩ አሊ ናቸው ።

የፕሮጅክቱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ መሰረት መቀጠሉን ገልጸው፤  ቀሪ ስራዎችን በተመሳሳይ ፍጥነትና ጥራት ድርጅቱ እንደሚያጠናቀቅ የሚጠበቅ መሆኑን አብራርተዋል ።

በፕሮጀክቱ ከተሰሩ የዝናብ ውሃ ማሰባሰቢያ ኩሬዎች ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል በሶማሌ ክልል ገላልሼ ወረዳ የሰመኔ ቀበሌ ነዋሪ አርብቶ አደር  አቶ ረሼድ ሹክሪ በሰጡት አስተያየት፤  ኩሬው ከመሰራቱ በፊት ውሃ ለማገኘት እስከ አስራ አምስት ኪሎ ሜትር ጎልጀኖ ድረስ ለመጓዝ እንገደድ ነበረ ብለዋል።

ኩሬው የተገነባው በንካ የተባለ አካባቢ መሆኑን ጠቅሰው፤ የእንስሳት ግጦሽ የሚገኝበት ቢሆንም ውሃ ባለመኖሩ ብቻ ሳይጠቀሙ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

የፕሮጀክቱ አስተዳደር ከመንገዱ ግንባታ  በተጓዳኝ  ለአርብቶ አደሩ ያጋጠመውን ድርቅ ለመቋቋም እንዲያገዝ የሰራው ኩሬ ለራሳችንም ሆነ ለቤት እንስሳቶቻች ለወራት የሚያቆየን ውሃ በአቅራቢያችን እንዲያናገኝ በማስቻሉ  ደስተኛ ነኝ ነው ያሉት።

በፕሮጀክቱ የስራ እድል ከተፈጠረላቸው  ሰዎች አቶ ተፈሪ መጎስ ፤ በፕሮጀክቱ የስራ እድል በማገኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸው፤ ከማህበረሰቡ ጋር ያለው ፍቅርና መረዳዳት ለሌሎች አርዓያነት ያለው ነው ብለዋል።

በአካባቢው ችግኝ በማትከልና የአንቡላንስ አገልግሎት ለህብረተሰቡ  በነፃ በመስጠት እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የፌዴራል መንግስት በመደበው  በጀት ከአንድ ሺህ አንድ መቶ በላይ ኪሎ ሜትር የሚሸፍን 16 አገናኝ አስፓልት መንገዶች ግንባታ በተለያየ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርን በመረጃ ምንጭነት ጠቅሶ የኢዜአ ሪፖርተር ከሥፍራው ዘግቧል።


Read More
None

የቅባት እህሎችን በስፋት ማምረት ለዘይት ምርት የዋጋ መረጋጋት የተሻለ አስተዋፅዖ እንዳለው ተጠቆመ፡፡

May 7, 2022

በቤአኤካ ስር ካሉ ፋብሪካዎች አንዱ ሆነው የኮከብቃናየዘይትፋብሪካበቀን 165 ቶንዘይትየሚያጣራ እናፋብሪካውየዘይትምርትለሕብረተሰቡበስፋትየማቅረብዓቅምያለውመሆኑ ተገለጸ

(ኢ ፕ ድ)


Read More
None

እጆች ሁሉ እንደ ወይዘሮ ዘመናይ ለተቸገሩ ወገኖች ይዘርጉ!

March 4, 2022

ባሕር ዳር: የካቲት 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ለረጂም ጊዜ የቆየ የኩላሊት ሕመም ያሰቃያቸዋል፣ የካንሠር ታማሚ መሆናቸውንም ነግረውናል። በሌላ በኩል ደግሞ ኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸው ስላለ መድኃኒት ይወስዳሉ። ወይዘሮ ዘመናይ በላይነህ በየእለቱ የሰቆቃ ሕይወት እየመሩ ያሉ የሁለት የልጆች እናት ናቸው። እሳቸው ሕክምና ተቋም ሄዶ የጤናቸውን ጉዳይ ለመከታተል ይቅርና ልጆቻቸውን በቅጡ ቁርስ መግበው ምሳ መድገም የሚያስችል አቅም የላቸውም።


Read More